የቴክኖሎጂ ፈጠራና ምርምር ሲፖዝየም በአቪዬሽን ዘረፍ የፈጠራ ሰራቸውን

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ ሴኔ 01/2015 ዓ/ም ባዘጋጀው የቴክኖሎጂ ፈጠራና ምርምር ሲፖዝየም በአቪዬሽን ዘረፍ የፈጠራ ሰራቸውን ያቀረቡ ተማሪዎች ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሰልጣን አሶሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት ጉብኝት አድርገዋል።

ጉብኝቱን ያሰጀመሩት የቴክኖሎጂ ሽግግር ልማት ዳይሬክቶሬት አቶ የሻምበል በዛብህ ሲሆኑ የአቪዬሽን ዘርፍ በረካታ አዳድሰ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ዘርፍ ቢሆንም የሀገር በቀል ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ድረሻ ግን አነሰተኛ ነው።ሰለሆነም ጉብኝቱ ለፈጠራ ባለቤቶች ትልቅ ጠቀሜታ ሰላለው በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

ዳይሬክቶሬቱም አክለውም ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሰልጣን አሶሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በቀጣይ ለሚኖረን ጊዜ በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል።

ሲቪል አቪዬሽን ታውረ ባለሙያ አንድነት በውሶ ሰለ አቪዬሽን ሙሉ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የፈጠራ ባለቤቶች የተሻለ ፈጠራ በማቅረብ በሀገረ አቀፈ ደርጃ ለሚካሄደው የፈጠራ ወድድር ላይ የተሻለ ነገረ ሰረተው ማቅረብ እንዳለባችው ገልጸዋል ።

ገለጻ ካደርጉ ባለሙያዎች መካከል ፖይለት፣በበረራ ተቆጣጣሪዎች ፣ፋየር ብርጌድ ባለሙያዎች እና የሜትሮሎጂ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ገለጻ ተደርጓላችዋል።

በጉብኝቱ ላይ የፈጠራ ባለቤቶች ጉብኝቱ ለጀመርናችው የፈጠራ ሰራዎች ለመጨረሰ እና አድሰ ፈጠራ ለመሰራት እንደሚያግዛችው ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *