የቤኒ/ጉ/ክ/መ/የሳይ/ቴክ/ኢን/ኮሚ/ኤጀንሲ የ2015ዓ/ም አጠቃላይ የሪፖርት ግምገማ እና በበጀት ዓመቱ ጥሩ የሰራ አፈፃፀም ላሳዩ ባለሙያዎችም የዕውቅና የማበረታቻ ሽልማት ሰነ-ስርዓት ተካሄደ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2015ዓ/ም አጠቃላይ የሪፖርት ግምገማ እና በበጀት ዓመቱ ጥሩ የሰራ አፈፃፀም ላሳዩ ባለሙያዎችም የዕውቅና የማበረታቻ ሽልማት ሰነ-ስርዓት ተካሄደ።

//////////////////////////////////////////////////////////////

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2015ዓ/ም አጠቃላይ የሪፖርት ግምገማ እና በበጀት ዓመቱ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላሳዩ ባለሙያዎችም የዕውቅናና የማበረታቻ ሸልማት ሰነ-ሰርዓት ተካሂዷል። በፕሮግራሙም ላይ የት/ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃፈር ሀሩን እና የኤጀንሲው ሀላፊ የሆኑት አቶ ተመሰጌን ሀይሉ ውይይቱን ያሰጀመሩ ሲሆን የ2015 ዓ/ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በኤጀንሲው የዕቅድ ባለሙያ በሆኑት በአቶ እንድሪስ የቀረበ ሲሆን ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ያሳየበት በመሆኑ በቀጣይም አመት ትኩረት በሚሰጣቸው ጉዳዬችን በመጠቆም የ2016 ዕቅድ ላይ ታቅደው መሰራት እንዳለባቸው አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በኤጀንሲው የተሻለ የስራ አፈጻጸም ላሳዩ ባለሙያዎችም የቁሳቁስና የሰርተፍኬት ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን 1ኛ ደረጃ የወጣው ባለሙያ ፍቃዱ ደሬሳ 2ኛ ደረጃ የወጣው ብረሀኑ ሽታነህ 3ኛ ደረጃ የወጣው ሙባረክ መሀመ ድ 4ኛ ደረጃ የወጣው አሰናቀ መኮነን 5ኛ ደረጃ የወጣችው ኬሪያ መሀመድ ሲሆኑ በቀጣይ አመትም በተነሳሺነትና በታታሪነት ለሚሰሩ ባለሙያዎች የሽልማትና የዕውቅና ስነ-ስርዓቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ተመስጌን ሀይሉ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *