የቤ/ጉ/ክ/መ/ሳ/ቴ/ኢ/ኮ/ኤጀንሲ ከፑል መ/ቤት ጋር በመሆን የብልፅግና ፓርቲ አባላት መፍጠንና መፍጠር በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ዉይይት አደረጉ።

የቤ/ጉ/ክ/መ/ሳ/ቴ/ኢ/ኮ/ኤጀንሲ ከፑል መ/ቤት ጋር በመሆን የብልፅግና ፓርቲ አባላት መፍጠንና መፍጠር በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ዉይይት አደረጉ።

#########################

(ሰኔ 23/2015ዓ/ም)የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የሳ/ቴ/ኢ/ኮ/ኤጀንሲ የብልፅግና ፓርቲ አባላት መፍጠንና መፍጠር በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሀገራዊ ሰነድ ላይ ዉይይት አደረጉ።

በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ሞሲሳ መሸሻ አቅራቢነት እና አወያይነት የቀረበዉ ሰነድ አብይ ርዕስ መፍጠን እና መፍጠር የሚል ሲሆን ንዑሳን ርዕሱ ደግሞ የወልን እዉነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ የሚል ነዉ።

አቅራቢዉ በመፍጠር መፍጠን በመፍጠን መፍጠር የሚሉ አባላቱን ለበጎ ተግባራት የሚያነሳሱ ንግግሮችን እያከሉ ከዚህ ቀደም የተከናወኑ ተግባራትን አሁን ያለበትን ደረጃ እና የወደፊቱን ብሩህ ተስፋ ህዝቡ ከአባላቱ የሚጠብቀዉን ዉጤት እና መሠል ጉዳዮችን በማንሳት ሰፊ ዉይይት የተደረገ ሲሆን ከምክንያት ይልቅ ዉጤት ላይ ትኩረት በማድረግ ሁሉም አባል ለሀገሩ እና ለህዝቡ የተሻለ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የሚያደርግ ዉይይት ተካሂዷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *