የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ የተዘጋጀ የቴክኖሎጂ ፈጠራና ምርምር ለሀገር ብልጽግና በሚል መሪ ቃል ሲምፖዚየም አካህል።
(ግ/በለስ መጋቢት 28/2015ዓ/ም)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ የተዘጋጀ የቴክኖሎጂ ፈጠራና ምርምር ለሀገር ብልጽግና ለማሳደግ ያለመ ሲምፖዚየም በመተከል ዞን በግልገል በለስ ከተማ አካሂዷል።
ኤጀንሲው ”የቴክኖሎጂ ፈጠራና ምርምር ለሀገር ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኝው በዚህ ሲምፖዚየም ላይ የመተከል ዞን ሁሉም ወረዳዎች እና ግ/በለሰ ከተማ አሰተዳድር የሚገኙ የ1ኛ እና 2ኛ ደርጃ ት/ቤት ተማሪዎች የፈጠራ ሰራቸውን አቅርበዋል።
በሲምፖዚየሙም በተማሪዎች የተዘጋጅ የእህል ወፍጮ፣ማንደጃ፣የሚጥሚጣ መፍጫ፣ገልባጭ መኪና እና የተለያዪ ማተርያሎች የፈጠራ ውጤቶች ቀርበዋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር አቶ ተመስጌን ሀይሉ የመክፈቻ ንግግር እና የሲምፖዚየሙን ዋና አላማ እናየፈጠራ የምርምር ባለቤቶችን ከማበሪታታት ባሻገር ለሀገር እና ለክልሉ ጠቀሜታ ያላችውን የፈጠራ እና የምሪምር ሰራዎችን ለማጠንከር መሆኑን ተናግርዋል።
ዋና ዳሬክተር አክለውም የመተከል ዞን እና የግ/በለሰ ከተማ አሰተዳድር በሚገኝ የመንግሰት ት/ቤቶች የሳይንስ ፈጠራ ክበባት መቋቋሙን የገለጹ ሲሆን፣ ሲምፖዚየሙን ሲካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግርዋል።
ከተሳተፉት 8 ውረዳ ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ ደርጃ የወጣው ተማር በረከት ደረሰ የፖውይ መንድር 7 ት/ቤት 2ኛ ደርጃ የውጣው ሀይለ አምላክ ሀብቴ የማንቡክ 1ኛ ደርጃ ት/ቤት 3ኛ ደርጃ የወጣው ሙአዝ ኢሳ የማንኩሽ ት/ቤት በአርያ መምህር መ/ር ገበየው አዱላ ሲሆኑ በሽልማቱ ደሰተኛ መሆናችውን ገልጸዋል።
በፖሮግራሙ ላይ በመተከል ዞን ሁሉም ወረዳዎችና በገ/በለሰ ከተማ አሰተዳደር የተሳተፉ የፈጠራ ባለቤቶች ማበረታቻ የሚሆን ሰረተፍኬት እና የዕውቅና ሸልማት በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና በዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በኩል ተበረክቶላቸዋል።