ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በአሶሳ ዞን ስር ለሚገኙ ወረዳዎች እና በአሶሳ ከተማ አስተዳደር

ቀን 16/06/2015 ዓ.ም

አሶሳ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በአሶሳ ዞን ስር ለሚገኙ ወረዳዎች እና በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ ለሁለት መምረያ ሀላፊዎች ፣ለስረዓተ -ትምህረት ባለሙያ እና ለአሶሳ ከተማ አሰተዳደር ስር ላሉ ለግል ት/ቤቶች ተወካዮች ባለድርሻ አካላት የሳይንስና ፈጠራ ክበባት እንቅሰቃሴ በፋይናንስ ለማበረታታትና ለመደገፍ እንዲያመች በተዘጋጀው መመሪያ ቁጥር 1/2015ዓ.ም ዙርያ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫና የውይይት መድረክ ተደረገ ።

////////////////////////////////////////////////////

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስጌን ሀይሉ በመክፈቻ ንግግራቸው በት/ቤቶች የተቋቋሙ የሳይንስና ፈጠራ ክበባቶችን ስለማጠናከርና በፋይናንስ ለመደገፍ የሚያስችል መመሪያ 1/2015ዓ.ም በሚል መዘጋጀቱንና ዛሬ ውይይት ተደርጎበት በተግባር እንዲሰራበት ከት/ቢሮና ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የገለጹ ሲሆን ኤጀንሲውም አጠቃላይ ገጽታ እና እስካሁን እየሰራ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ አብራርተዋል።

በመቀጠልም የቴክኖሎጂ ሽግግር ባለሙያ የሆኑት አቶ አይቸው ሲሳይ የሳይንስና ፈጠራ ክበባቶችን ለመደገፍ የወጣውን መመሪያ በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የማጠቃለያ ውይይት መድረኩንም የት/ቢሮ ም/ ሀላፊ የሆኑት አቶ ጃፈር ሀሩን እና የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስጌን ሀይሉ የመሩት ሲሆን በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን የተቋሞች ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በቀጣይ ለሚካሄደው የሳይንስና ፈጠራ ሲምፖዚየምም የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *