የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ እና የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲ/ሰ/ቢሮ ጋር በመተባበር ከዚህ በፊት በሀላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ አመራሮችን የመሸኘት እና አድስ የተሾሙ አመራሮችን የመቀበል ፕሮግራም አካሄዱ።
/////////////////////////////////////////////////////////////////
(አሶሳ ሀምሌ 30/2015/ዓ/ም)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ እና የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲ/ሰ/ቢሮ ጋር በመተባበር ከዚህ በፊት በሀላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ አመራሮችን የመሸኘት እና አድስ የተሾሙ አመራሮችን የመቀበል ፕሮግራም አካህደዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲ/ሰ/ቢሮ ዋና የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት አቶ ሀሽም መልዕክት አሰተላልፈዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም የ2015 ዓ/ም የተሰሩ ስራዎችን እና የተቋሙን አጠቃላይ ገጽታ ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች አብራርተዋል።
ከዚህ በፊት ለነበሩ አመራሮችም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ እና የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲ/ሰ/ቢሮ ስጦታ አበርክቶላቸዋል።
ሰጦታ የተበረከተለቸው አመራሮችም እንደተናገሩት ከሆነ ከዚህ የበለጠ ለሚሄዱበት ቢሮ ለመሰራት እንደሚያነሳሳቸው እና የተበረከተላቸው ስጦታ መቸም የማይረሳቸው መሆኑን ተናገሩ።
አድስ በሹመት የመጣው አመራር የቤ/ጉ/ክ/መ/ምክትል ፕሬዝዳንት እና የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲ/ሰ/ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ጌታሁን አብዲሳ እንደገለጹት አሁን አድስ ለመጣነው አመራሮች ትልቅ የቤት ስራ እንደተጣለባቸው ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም የተጣለባቸውን ሀላፊነት በብቃት ለመወጣትና ተባብሮ ለመሰራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የቤ/ጉ/ክ/መ/የብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር እና የቤ/ጉ/ክ/መ/አፈ ጉባኤ ዶክተር ተመስጌን ዲሳሳ እና ሌሎችም አመራሮች በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል።
የቤ/ጉ/ክ/መ/የሳ/ቴ/ኢ/ኮ/ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ተመስጌን ሀይሉ ከክ/ሲ/ሰ/ቢሮ ሀላፊዎች ጋር በቅርበት በመወያየትና በመመካከር በተቋማትና በሰራተኞች መካከል ቅሬታዎች እንዳይፈጠሩና ሲፈጠሩም አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የነበራቸው ቁርጠንነት ቀላል አለመሆኑን በመግለጽ ኤጀንሲው ይህንን ፕሮግራም በማዘጋጀት የድርሻቸውን የተወጡ መሆኑን ገልጸዋል::