በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ እና መንጌ ወረዳ የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ይታያል በላይ ገለጹ።
(አሶሳ ሚያዝያ 2/08/2017ዓም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ እና መንጌ ወረዳ የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ የግንዛቤ ማስጨበጫ በስፋት መሰጠቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ይታያል በላይ ገለጹ።
በፕሮግራሙ ላይ በወረዳዎች የቴክኒካል ኮሚቴና የኦፕሬሽን ቲም የተቋቋመ ሲሆን ሰልጠናው በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ከኢንዱስትሪ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ኮርሶች ጨምሮ በኦንላይን ኮዲንግ በዌብ ፕሮግራሚንግ፣በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት የሚያስጨብጥ መሆኑንና ለምንገነባው ዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።
የኤጀንሲው ዳይሬክተር አክለውም ዲጂታል ቴክኖሎጂ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው ይህን ኢኒሸቲቭ አብረውን ከሚሰሩ ተቋማት አንዱ የሆነው የክልላችን ትምህርት ቢሮ በአሁኑ ዘመቻ ለዚህ ስራ ውጤታማነት ላደረጉት እገዛ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ይታያል በላይ ለሴክተር መስሪያቤት ሰራተኞች፣ ለወረዳ አመራሮች፣ ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቶ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰው ዲጂታል ቴክኖሎጂ የወቅቱ የመንግስት ከፍተኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አስገንዝበዋል።የኤጄንሲው ባለሙያ ወ/ሮ ፋጡማ አህመድ በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ የፕሮግራሙ ዓላማ ወጣቱን ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲሳተፍ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
በተያያዘ የኤጀንሲው ባለሙያና የኢኮቴ መሰረተ ልማት ዳይሬክተር ተወካይ ና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አይቸው ሲሳይ የመክፈቻ ንግግሩ ላይ ስልጠናው ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ቴክኖሎጂ መሠረታዊ ክህሎት እንዲኖረው የሚያደርግና የተቋማትን አሰራር አዘምኖ የስራ ዕድሎችንም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ቀናት የግንዛቤ ማሰጨበጫ ሰልጠናው በቀሩት ሁሉም ወረዳዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።


