የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኤጄንሲ ባለሞያዎች በአቡራሞ ወረዳ በመገኘት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጡ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኤጄንሲ ባለሞያዎች በአቡራሞ ወረዳ በመገኘት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጡ።

ኢንሼቲቭ የወረዳውን የስትሪንግ :የቴክኒክ ኮሚቴዎች : የኦፕሬሽናል ቲም የተቋቋመ ሲሆን ለሴክተር መስሪያቤቱ ሰራተኞችና አቡራሞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች

(አሶሳ ሚያዚያ 8/2017) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ ባለሙያዎች በአቡራሞ ወረዳ በመገኘት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጡ።

የኤጀንሲ ባለሙያዎች አቡራሞ ወረዳ በመገኘት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የወረዳው የቴክኒክ ኮሚቴዎችን እንዲሁም የኦፕሬሽናል ቲም ያቋቋሙ ሲሆን ለሴክተር መስሪያ ቤት ሰራተኞችና ለአቡራሞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።

የአቡራሞ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ቄስ ደርቤ ተገኝ የመክፈቻ ንግግር እና ፕሮግራሙን አስመልክቶ መልዕክት አሰተላልፈዋል። በግንዛቤ ማስጨበጫው ወቅት የኤጀንሲው ባለሙያ አቶ አይቸው ሲሳይ እንደተናገሩት የፕሮግራሙ ዓላማ ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ቴክኖሎጂ መሠረታዊ ክህሎት እንዲኖረው የሚያደርግና የተቋማትን አሰራር ለማዘመንና የስራ ዕድሎችንም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልጠናው በፍላጎት ላይ የተመሰረተ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው፣ ከኢንዱስትሪ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ኮርሶች በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው ይህም በፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት የሚያስጨብጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተዘጋጀውን የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችል ነጻ የኦንላይን ሥልጠና ለመውሰድ በዚህ ሊንክ https://ethiocoders.et/ ገብተው ይመዝገቡ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *