የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ናየኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስትር ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ላይ ክልላችንን ወክለው የተላኩ ተማሪዎች እና መምህራኖች ተሸላሚ ሆኑ !!!
///////////////////////////////////////////////////////
(ህዳር 8 /2016 ዓ/ም አሶሳ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ናየኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስትር ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ላይ ክልላችንን ወክለው የተላኩ ተማሪዎች እና መምህራኖች ተሸላሚ ሁነዋል።
የኤጀንሲው የቴክኖሌጂ ሽግግር ልማት ዳይሬክተር አቶ የሻምበል በዛብህ እንደገለጹት ይህ ውጤት መመዝገቡ በዘርፉ ከዝህ የተሻለ ለዘርፉ ትኩረት ሰተን እንድሰራ መነሻ ይሆናል ብለዋል ።ዳይሬክተሪ አክለውም ሁሉም የሚመለከተው ባለድረሻ አካል የሳይንሰ ቴክኖሌጂ ፈጠራ ክበብ በመደገፍ በቀጣይ የተሻለ ውጤት እንድመጣ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በፖሮግራሙ ላይ ከተሳተፉ 15 (አሰራ አምስት) ተወዳዳሪዎች መካከል 2 (ሁለት) ተማሪዎች እና አንድ (1) መምህር ተሸላሚ በመሆን አጠናቀዎል።
የተሸላሚ ተማሪዎች እና መምህረ ሰም ዝርዝር
1. ተማሪ ሙባረክ ሰይድ 2ኛ በመውጣት የላፕቶፕ
2. ተማሪ ሄለን ተካልኝ ታብሌት እና
3. መ/ር ታከለ ታደሰ ላፕቶፕ ተሸልመዋል።
በዉድድሩ የተሳተፉ ተወዳዳሪዎች እንደተናገሪት ዉድድሪ የተሻለ ተሞክሮ የወሰድበት መሆኑ እና ለቀጣይ ለሚደረገው ሀገር አቀፍ ዉድድር ተዘጋጂተው እንደሚመጡ ተናግረዎል።