የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ ማናበብ ለግ/በለሰ ከተማ አስተዳደር እና በመተከል ዞን ስር ለሚገኙ የአይሲቲ ባለሙያዎች እና የሰርአተ ትምህርት ባለሙያዎች ጋር እቅድ የማናበብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ ማናበብ ለግ/በለሰ ከተማ አስተዳደር እና በመተከል ዞን ስር ለሚገኙ የአይሲቲ ባለሙያዎች እና የሰርአተ ትምህርት ባለሙያዎች ጋር እቅድ የማናበብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

///////////////////////////////////////////////////////

(መሰከረም 25 /2015 ዓ/ም አሶሳ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ ማናበብ ለግ/በለሰ ከተማ አስተዳደር እና በመተከል ዞን ስር ለሚገኙ የአይሲቲ ባለሙያዎች እና የሰርዓተ – ትምህርት ባለሙያዎች ጋር የዕቅድ ማናበብ የወይይት መድረክ ተካሂዷል።

በኤጀንሲው የአቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ፍቃዱ ደሬሳ የተቋሙን የ2016 ዓ/ም መሪ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተድርጎበታል። የቴክኖሎጂ ሽግግር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የሻምበል በዛብህ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ክበባቶችን በማቋቋምና በማጠናከር ለመስራት እንዲያስችል የሚያደርጉ መመሪያና ዋና ዋና ተግባሮች ላይ የግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነዶችን አቅረበዋል። በውይይቱም ላይ ለተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ተመሰጌን ሀይሉ በዙም ሚቲንግ/ZOOM MEETING/ ተገቢውን ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የተቋሙ የ2016 ዓ/ም የትኩረት አቅጣጫዎችንም አሰቀምጠዋል። የኤጀንሲው ሀላፊ አክለውም የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ስኬቶች እንደተሞክሮ በመውሰድ ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ 2016 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ስኬታማነት በማቀድ በመተግበርና ሪፖርት በማድረግ ካለፈው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት ሁሉም በየደረጃው በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ተሳታፊዎቹም በበኩላቸው ስራዎችን ተናበውና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ለተግባራዊነቱ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

#የኤጀንሲዉ ማህበራዊ ሚድያዎች

ድህረ-ገጽ/Website:- www.bgrsstica.gov.et

ኢሜል/Email:-bgrsstica@gmail.com

ቴሌግራም/Telegram Channel:-@bgrsstica1

ፌስቡክ/Facebook Page:-@bgsstica

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *