በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስ የሳይንስ፣ቴክኖሎጅና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንስ የተሰራው የኮሌጁ ዌብሳይትና ዳታ ቤዝ ርክክብ ተካሂዷል።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስ የሳይንስ፣ቴክኖሎጅና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንስ የተሰራው የኮሌጁ ዌብሳይትና ዳታ ቤዝ ርክክብ ተካሂዷል። በርክክቡ ወቅት የኮሌጁ ዲን አቶ ብዙአየሁ ሳንቢት ፈጣን የሆነ የመረጃ ፍሰት ባለበት ጊዜ እንደመሆናችን ኮሌጁ ከጊዜው ጋር እኩል መጓዝ አለበት፣አለም መረጃን እጅግ ፈጣን እና በዘመነ መንገድ እያደረሰ ይገኛል በመሆኑም ኮሌጁ ጊዜው የሚጠይቀውን የመረጃ ማድረሻ መንገድ መከተል አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል ብሏል። ማንኛውም ሰው የትኛውም ቦታ ሆኖ ስለኮሌጁ የሚፈልገውን መረጃ በቀላሉ ከኮሌጁ ዌብሳይት ማግኘት ይችላል ያሉት የኮሌጁ ዲን መረጃ ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ ተማሪዎች በኮሌጁ ዌብሳይት ገብተው የሚጫኑ ሞጅሎችን፣ማስተማሪያ መፅሀፍቶችን ማንበብ እና ማውረድ ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋል። ከዌብሳይቱ በተጨማሪ ተማሪዎች ኦንላይን የሚመዘገቡበት፣ውጤታቸውን የሚያዩበት ሲስተምም ርክክብ ተደርጓል። የኮሌጁ ዲን ዌብሳይቱን ለሰሩት የክልሉ ሳይንስ፣ቴክኖሎጅና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ ባለሙያዎች እንዲሁም አመራሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ማንኛውም ሰው ወደ ኮሌጁ ዌብሳይት www.bgrsgbcte.edu.et በመግባት ስለኮሌጁ መረጃ ማግኘት ይችላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *