ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ ለክልል ሴክተር መ/ቤቶች እና ለኤጀንሲው አይሲቲ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የኢኮቴ መሳሪያዎች አድቫንስድ ጥገና ሰልጠና ተጠናቀቀ።
//////////////////////////////////////////////////////////////
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩንኬሽን ኤጀንሲ ለለክልል ሴክተር መ/ቤቶች እና ከኤጀንሲ አይሲቲ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የኢኮቴ መሳሪያዎች አድቫንስድ ጥገና ሰልጠና ተጠናቋል። ሰልጠናዉ ለተከታታይ 4 ቀን የቆየ ሲሆን ለክልል ፈይናንስ ቢሮ:ለክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን : ለአሶሳ ሆስፒታል: ለክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ: ለክልሉ ገ/መ/አ/ኢንቨስትመንት ቢሮ:ለክልሉ ስፖርት ኮሚሽን እና ለኤጀንሲዉ አይሲቲ ባለሙያዎች የኢኮቴ መሳሪያዎች ኮምፒውተር: ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን አድቫንስ ጥገና ስልጠና መስጠት እና ተያያዠ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መሆኑን የኤጀንሲው ሀላፊ የሆኑት አቶ ተመሰጌን ሀይሉ ገልጸዋል።
የኤጀንሲው ሀላፊ አክለውም ከስልጠናው በሚያገኙት እውቀት እና ክህሎት ተጠቅመው በቢሮአቸው ያሉትን አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የኢኮቴ መሳሪያዎች ኮምፒውተር : ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሸን በመጠገን የመንግስትን ወጪ መቀነስ እንደሚቻል ተናግረዋል።