(አሶሳ ነሀሴ/2/2015 ዓ/ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሌጂና ኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2016 ዓ/ም በጀት አመት በውጤት ተኮር የተቃኘ አመታዊ እቅድ ግምገማ ተጠናቋል።
በኤጀንሲው እቅድ ዝግጂት ባለሙያ አቶ እንድርስ አሊ የ2016 ዓ.ም እቅድ ቀርቦ ውይይት ተድርጎበታል።
ውይይቱን ያሰጀመሩት የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ተመሰጌን ሀይሉ እንደተናገሩት የ2016 ዓ/ም እቅድ ሁሉም ዳይሬክቶሬት እና ባለሙያዎች እቅዳችውን አቅደው ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው እና ሁሉም ባለሙያዎች ተቋሙ የሚያከናውናቸውን ተግባራቶች ማወቅ እንዳለባቸውና በክልላችን ሳይንስና ቴክኖሎጂን ሊያሳድጉ በሚችሉ ተግባራት ላይ በሰፊው ታቅዶ መሰራት እንዳለበትና በዘንድሮው ዓመት ካለፉት ዓመታች በተሻለ ሁኔታ አቅደን ለመተግበር የሚያስችለንን ተግባራት አቅደው እንዲሰሩና ገንቢ አስተያየቶችን እንዲሰጡ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ለተከታታይ ሁለት ቀን ዕቅዱን በመገምገምና ገንቢ ሀሳቦችን በመስጠት ንቁ ተሳትፎ የተደረገበት ሲሆን ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎችም የየድርሻቸውን በማቀድ ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ተናግረዋል።