የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ይታያል በላይ ከኢፌድሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ እና ስቴት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ።
በውይይቱ ላይ ዶክተር በለጠ ሞላና ሚኒስተር ዴኤታው ዶ/ር ባይሳ በዻዻ፣ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ፣እንዲሁም የጽህፈትቤት ሃላፊው አቶ ልኡል ስዩም ጋር በክልላችን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙርያ በስፋት መክረዋል።
በውይይታቸው በክልሉ ያለውን ከፍተኛ የአሳ ምርት፣የወርቅ ምርት፣ የድንጋይ ከሰል፣የእምነበረድ፣የእጣን ምርት፣የቀርቀሃ ምርትና ሰፊ ለም የእርሻ መሬት በቴክኖሎጂ የታገዘ ባለመሆኑ ከዘርፉ የሚጠበቀው ውጤት አለመገኘቱን አንስተው በሚኒስቴር መስሪያቤቱ፣በፕሮጀክቶችና አለም አቀፍ ድርጅቶች ክልሉ በቴክኖሎጂ ቢታገዝ ሙሉ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድር የሚችል ሃብት መኖሩን አስረድተዋል።
ይህን ተከትሎ ክቡር ሚኒስትሩና ሚኒስትር ዴኤታዎች በቅርቡ ወደ ክልሉ እንደሚመጡና ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር እንደሚወያዩ አቶ Yitayal Belay Mekonen ገልጸዋል።
