የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2015 የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ ከክልል አይሲቱ ባለሙያዎች ጋር እቅድ የማናበብ የወይይት መድረክ ተካሄደ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2015 የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ ከክልል አይሲቱ ባለሙያዎች ጋር እቅድ የማናበብ የወይይት መድረክ ተካሄደ።

///////////////////////////////////////////////////////

(መሰከረም 8/2015 ዓ/ም አሶሳ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሳይንስ ቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሸን ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲ የ2015 የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2016 በጀት አመት አመታዊ እቅድ ከክልል አይሲቱ ባለሙያዎች ጋር እቅድ የማናበብ የወይይት መድረክ ተካሂዷል።

በኤጀንሲው እቅድ ዝግጂት ባለሙያ አቶ እንድርስ አሊ የተቋሙን 2015 አ/ም እቅድ አፈጻጸም ሪፓርት እና የ2016 ዓ/ም መሪ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተድርጎበታል። በውይይቱ ላይ የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ተመሰጌን ሀይሉ የመክፈቻ ንግግር እና የተቋሙን አጠቃላይ ገጸታ አቅርበዋል። የኤጀንሲው ሀላፊ አክለውም የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ስኬቶች እንደተሞክሮ በመውሰድ ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ 2016 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ስኬታማነት መዘጋጀት አለብን ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው ስራዎችን ተናበውና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ለተግባራዊነቱ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *