በክልሉ በሳይንስ እና ተክኖሎጂ ዘርፍ በፈጣራ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ህልማቸው እውን እንዲሆን እንደሚሰራ የክልሉ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በክልሉ በሳይንስ እና ተክኖሎጂ ዘርፍ በፈጣራ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ህልማቸው እውን እንዲሆን እንደሚሰራ የክልሉ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

(አሶሳ፣ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም)

አለም አሁን ላይ ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ ከፍተኛውን አስተዋጾኦ ያበረከተው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ዘርፍ ሲሆን በኢትዮጵያ ዘርፉ ገና በጅማሮ ላይ የሚገኝ ነገር ግን ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴዎች እየታየበት ያለ ዘርፍ ነው ።

በተለይ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ የፈጠራ ተስእጦ ያላቸው ወጣት ተማሪዎች በተለያዩ ጊዜያት የሚያሳዩት የፈጠራ ስራ ውጤቶች በዘርፉ ላይ በትኩረት ቢሰራ ሃገሪቱ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ዘርፍ ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ የምትችል መሆኑን ከወዲሁ የሚያመላክት ነው።

በአሶሳ ከተማ የአሶሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ፋሮ አንደኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ዘርፍ ተማሪዎች እየሰሩት ያለው ስራዎች በክልሉ በዘርፉ ላይ ተስፋ ሰጪ የምርምር ስራዎች መኖራቸውን አመላክተዋል።

በፋሮ ትምህርት ቤት የ6ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ተማሪ ሄለን እና በረከት በኮምፒውተር ሳይንስ የፈጠራ ስራ የትምህርት ቤታቸውን ድህረ ገጽ በመፍጠር ተማሪዎችም ሆነ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ስለ ፋሮ ትምህርት ቤት በቀላሉ መረጃ የሚያገኙበትን የፈጠራ ስራ የሰሩ ባለ ምጡቅ አእምሮ ባለበቶች ናቸው።

ተማሪዎቹ እንደመሚናገሩት ለፈጠራ ስራቸው መነሻ የሆነው በትምህርት ቤቱ የሚስተዋለው የመጻህፍት እጥረት ሲሆን ተማሪዎች ድህረ ገጹን በመጠቀም የፈለጉት አይነት መጻህፍት ማግኘት እንዲችሉ የሚያግዝ የፈጠራ ስራቸው እንደሆነ ነው የሚናገሩት።

በዚህ የፈጠራ ስራቸው ተማሪዎቹ ከክልሉ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ እውቅና እንደተበረከተላቸው ይናገራሉ።

ሌላኛው በአሶሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ ብርሃኑ ደግሞ የአከባቢውን ማህበረሰብ ችግር ይፈታሉ ያላቸው ከ4 በላይ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት ለእይታ ያበቃ ባለ ራእይ ታዳጊ ወጣት ነው ።

ተማሪው በአከባቢው የሚነኙ ቁሳቁሶችን በመጠቀም እናቶች ጤፍ ሲያበጥሩ የሚደርስባቸውን የስራ ጫና ማስቀረት የሚያስችል ፣ የማህበረሰቡ የውሃ ቧንቧ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን የውሃ ብክነት ማስቀረት የሚያስችል እንዲሁም ሌቦች የግለሰቦች እና ተቋማትን ለመዝረፍ ሙከራ ሲያደርጉ ቀድሞ መረጃ መስጠት የሚችል እና ሌሎች የፈጠራ ስራዎችን በመፍጠር ከኤጀንሲው እውቅና የተቸረ የፈጠራ ባለበት ነው።

ሁሉም የፈጠራ ባለበቶች እንደተናገሩት መነሻቸው በአከባቢያቸው የሚመለከቱት ችግሮች እንደሆነ ገልጸው ወደ ፊት ህልማቸው እውን እንዲሆን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

የክልሉ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኤጀሲ ዋና ዳይረክቴር አቶ ተመስገን ሃይሉ እንዳሉት በክልሉ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ዘርፍ በርካታ ባለተስእጦ ወጣቶችን ለማፍራት በተደረገው ጥረት ወደ ፊት በዘርፉ ከክልሉ አልፎ ለሃገር ከፍተኛ አስተዋጾኦ የሚያበረክቱ ወጣቶችን መለየት መቻሉን ተናግሯል።

የወጣቶቹ ራእይ እውን እንዲሆን ተቋሙ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል ያሉት አቶ ተመስገን በዚህም የፈጠራ ባለበቶችን ለመደገፍ እና ለማበረታታት የሚያስችል መመሪያ 1/2015 መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ለፈጠራ ስራቸው አቅም የሚፈጥር የልምድ ልውውጥ ከተለያዩ ተቋማት ጋር እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑንም የገለጹት አቶ ተመስገን በክልል ደረጃም ቢሆን የወጣቶች የፈጠራ ስራዎች እዲጎበኙ ኤግዝቢሽኖች እየተካሄዱ መሆናቸውነን አቶ ተመስገን ተናግረዋል።

በጣሰው እጀታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *